በቀጣዮቹ ዓመታት የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ዓለም አቀፍ ተጽዕኖዋን በሚያሳድግ መልኩ ይቃኛል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing በቀጣዮቹ ዓመታት የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ዓለም አቀፍ ተጽዕኖዋን በሚያሳድግ መልኩ ይቃኛል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN- መስከረም 25/2019 ዓ.ም

በቀጣዮቹ ዓመታት የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ዓለም አቀፍ ተጽዕኖዋን በሚያሳድግ መልኩ ይቃኛል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰይመዋል።

በምክር ቤቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሀገሪቱን ወቅታዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የቀጣናዊ ጂኦፖለቲካዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸውም፤ ባለፉት ምርጫዎች ከ54 ሚሊየን በላይ ዜጎች በዲሞክራሲያዊ ሂደቱ ላይ በመሳተፍ ላሳዩት ቁርጠኝነት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በማንኛውም ምርጫ አሸናፊና ተሸናፊ ፓርቲ ሊኖር ይችላል፤ በኢትዮጵያ ግን አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ አይኖርም ሲሉ አረጋግጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገር የሚገጥማትን ፈተና መሻገር የምትችለው ህዝቦች እንደ ወንድማማች እጅ ለእጅ ተያይዘው እኩል መራመድ ሲችሉ ብቻ እንደሆነ አስምረውበታል።

አሁን ያለው የዓለምና የቀጣናው ጂኦፖለቲካዊ ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ እየተቀየረ መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ፣ በቀይ ባህርና በህንድ ውቅያኖስ ስትራቴጂካዊ መገናኛ ላይ የምትገኝ በመሆኗ ይህንን እድልና ፈተና ለመወጣት ቀድሞ መዘጋጀት የትውልዱ ትልቅ አደራ መሆኑን ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፤ በቀጣዮቹ ዓመታት የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ዓለም አቀፍ ተጽዕኖዋን በሚያሳድግ መልኩ ይቃኛልም ብለዋል፡፡

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review