በከተማችን የስፖርት መሠረተ ልማትን ማስፋታችን ለወጣቶችና ለታዳጊ ልጆች ጤናማ፣ ተስፋ የሞላበትና የስኬት መንገድ እየከፈትን ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – ጥቅምት 8/2019 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ የቄራ አልማዝዬ ስፖርት ሜዳ እና ሥልጠና ማዕከልን በዘመናዊ መልኩ መልሰን ገንብተን ለስፖርት ቤተሰቡና ለወጣቶቻችን ማበርከታችን ትልቅ ደስታ ነው ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች አክለውም፣ ይህ ሜዳ በታሪኩ ለኢትዮጵያ ኩራት የሆኑ ታዋቂ ስፖርተኞችን አፍርቷል። ዛሬም ከዚህ ሜዳ አዳዲስ የስፖርት ጀግኖች፣ የሀገር ኩራቶችና የድል ባለቤቶች እንዲፈልቁ እድሉን እየፈጠርን ነው ብለዋል።

ሜዳው ከዚህ ቀደም በአቧራና በጥሻ ተውጦ፣ ለስፖርት እንቅስቃሴ ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ቆይቶ ነበር። ዛሬ ግን በድጋሚ ለወጣቶቻችን፣ ለታዳጊዎችም አካታች ሆኖ ስለተገነባ የችሎታቸው መድረክና የሕልማቸው ተስፋ ሆኖ ተመልሷል ብለዋል።

በከተማችን የስፖርት መሠረተ ልማትን ማስፋታችን ለወጣቶችና ለታዳጊ ልጆች ጤናማ፣ ተስፋ የሞላበትና የስኬት መንገድ እየከፈትን መሆናችን ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች፣ ከዚህ ሜዳ በሀገርና በዓለም መድረክ የሚያበሩ ታላላቅ ስፖርተኞች ይፈልቃሉ የሚል እምነት አለን! ብለዋል፡፡

ይህ የጋራ ሀብታችን ነው። እንጠብቀው፤ እናልማበት፤ በጋራም እናሳድገው! ለወጣቶቻችን ዕድል እንፍጠር፤ ለሕልማቸው መንገድ እንክፈት፤ ለኢትዮጵያም አዲስ የድል ታሪክ እንጻፍ! ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review