ሀገራችን ያልተሞከሩ ግዙፍ ልማቶችን በማከናወን በየጊዜው ወደ ላቀ ደረጃ እየተሸጋገረች ትገኛለች -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

You are currently viewing ሀገራችን ያልተሞከሩ ግዙፍ ልማቶችን በማከናወን በየጊዜው ወደ ላቀ ደረጃ እየተሸጋገረች ትገኛለች -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

AMN – ሰኔ 16/2018 ዓ.ም

ሀገራችን በራሷ አቅም ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመገንባት፣ ያልተሞከሩ ግዙፍ ልማቶችን በማከናወን በየጊዜው ወደ ላቀ ደረጃ እየተሸጋገረች ትገኛለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፣ “ኢትዮጵያ ታከናውናለች” በተሰኘው ብሔራዊ ጉባኤ ላይ በመገኘቴ ታላቅ ክብር ይሰማኛል ብለዋል።

‎“ከለውጥ ወደ ዘላቂ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ፣ በየደረጃው የተጓዝንበትንና አሁን የደረስንበትን መንገድ መለስ ብዬ እንድቃኘው አድርጎኛል ሲሉ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በመልዕክታቸው እንዳሰፈሩት ፣ ሀገራችን በራሷ አቅም ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመገንባት፣ ያልተሞከሩ ግዙፍ ልማቶችን በማከናወን በየጊዜው ወደ ላቀ ደረጃ እየተሸጋገረች ትገኛለች።

እነዚህ ሁሉ በአጋጣሚ የተገኙ ድሎች ሳይሆኑ በመደመር መንፈስ ላይ ተመስርተው ፣ ዘላቂ ለውጥ የሚመጣው በጋራ በመቆም ነው ፤ በሚል ጽኑ እምነት የተወሰዱ፣ በቆራጥ ውሳኔዎች የተገኙ ውጤቶች ናቸው ብለዋል።

የጀመርናቸው ለውጦች በራሳቸው የመጨረሻ ግብ አይደሉም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ ይልቁንም ከእኛ በኋላ ለሚመጡት ተከታታይ ትውልዶች የምንጥለው ጠንካራ መሠረት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

‎ሀገርን መገንባት በአንድ ትውልድ ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን የሁላችንም የጋራና ቀጣይነት ያለው ሥራ በመሆኑ፤ በዚህ ጽኑ እምነት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይህንን መንፈስ ይዞ ወደፊት እንዲጓዝ፣ የተቀበለውን ወረት አግዝፎ ይበልጥ ወደ ላቀ ከፍታ እንዲያመራ ጥሪዬን አቀርባለሁ! ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review