AMN- ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም
ህገወጡ የህወሓት ቡድን የትግራይ ክልል ህዝብን ጸረ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ በማፈን ድምጹ እንዳይሰማ እና ህዝቡን የመነጠል ሥራ ሲሰራ የነበረ መሆኑን የጂኦ ፖለቲክስ ተንታኝ መሐመድ ሲራጅ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የጂኦ ፖለቲክስ ተንታኝ መሐመድ ሲራጅ (ዶ/ር) ከኤ ኤም ኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ህገወጡን የህወሓት ቡድን እና የትግራይ ክልል ህዝብን ለይቶ ማየት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የትግራይ ህዝብ ላለፉት በርካታ ዓመታት በኢትዮጵ ታሪክ ውስጥ የራሱን አሻራ ሲያሳርፍ የነበረ እና አሁንም እያሳረፈ ያለ ህዝብ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ህገወጡ የህወሓት ቡድን በህዝብ ስም ውስጥ ተደብቆ የኖረ ህዝብን ጸረ ዲሞክራሲ በሆነ መልኩ በማፈን ድምጹ እንዳይሰማ ህዝቡን የመነጠል ሥራ ሲሰራ የነበረ ነው ብለዋል፡፡
ቡድኑ የትግራይ ክልል ህዝብ በኢኮኖሚ ስብራት ውስጥ እንዲቆይ ሲሰራ እንደቆየም አንስተዋል፡፡
ህገወጡ ሕወሓት የዘራውን በትክልል እያጨደ ነው ያሉት መሐመድ ሲራጅ (ዶ/ር)፤ ቡድኑ እየጠፋና እየከሰመ እንዲሁም ከህዝብ እየተነጠለ ስለመሆኑም አስረድተዋል፡፡
ቡድኑ በክልሉ በርካታ ጥፋቶችን ሲፈጽም እንደነበር በመግለጽ በህገ ወጡ ህወሓት ውስጥ ያለው ክፍፍልም የጋራ ውሳኔውን እና የጋራ አቅሙን አዳክሞታል ብለዋል፡፡
በክልሉ አሁን ላይ የትግራይ የሰላም ሃይል ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት የትግራይ ክልልን ህዝብ ሰላም እያስጠበቁ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡
የሻምበል ምህረት