የብሉምበርግ ዓለም አቀፍ የመንገድ ደህንነት ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሄደ

You are currently viewing የብሉምበርግ ዓለም አቀፍ የመንገድ ደህንነት ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሄደ

AMN- ኅዳር 1/2019 ዓ.ም

ከ30 የዓለም ሀገራት የተውጣጡ ተሳታፊዎች የተገኙበት የብሉምበርግ ፊላንትሮፒ ኢኒሸቲቭ ፎር ግሎባል ሮድ ሴፍቲ ዓለም አቀፍ የመንገድ ደህንነት ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ምክትል ከንቲባ እና የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ፤ መዲናዋ በአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷ አሁን ላይ በርካታ የመንገድ ግንባታዎችን ጨምሮ ጠንካራ የከተማ ልማት ሥራዎችን እያከናወነች መሆኗን ገልጸዋል።

የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ተፈራ ሞላ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ አዲስ አበባ በአህጉሪቱ ከተሞች በተሻለ የመንገድ መሰረተ ልማት በመገንባቷ ተሸላሚ መሆኗን አንስተው፣ ጉባኤው ይህንኑ ተምሳሌታዊ ስኬት ለሌሎች ሀገራት ለማጋራት የተሰናዳ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህ ጉባኤ ላይ በአዲስ አበባ እየተከናወነ የሚገኘው የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ ዘርፈ-ብዙ ጥቅምና በትራፊክ አደጋዎች ቅነሳ ላይ ያስገኘው ውጤት አዎንታዊ ምላሽ ያገኘ ሲሆን፤ የከተማዋን የቀድሞ የመንገድ ሁኔታ የሚያውቁ የውጭ ሀገር ተሳታፊዎችም የተመዘገበው ለውጥ አስደናቂ መሆኑን መስክረዋል።

በመሆኑም ይህ የመንገድ መሰረተ ልማት ማሻሻያና የደህንነት ትኩረት በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተመላክቷል።

በየምስራች ተረክበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review