AMN- ኅዳር 12/2019 ዓ.ም
ሁለንተናዊ ብልጽግናችንን ለማረጋገጥ በምናደርገው ጉዞ ጥራት የማንደራደርበት ቁልፍ ጉዳያችን ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ለ13ኛ ጊዜ ዛሬ በተካሄደው ሀገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ ከኢፌዲሪ ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የበላይ ጠባቂ አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ጋር ተገኝተናል ብለዋል።
ያለ ጥራት የሚታሰብ ዕድገት የለም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በመሆኑም ምርትና አገልግሎቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ በሚያደርግ የጥራት ልክ ማቅረብ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው በማለት አክለዋል።
የመደመር መንግሥት የሀገራችንን ሁለንተናዊ አቅም አቀናጅቶ በመጠቀም በሁሉም ዘርፎች የጥራት መሠረተ ልማቶችን መገንባትና የጥራት ባህልን በማስረጽ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ሲሉም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅትም በሀገራችን የጥራት ግንዛቤን ለማሳደግና በምርትና አገልግሎት የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ተቋማትን ለማበረታታት በየዓመቱ የሚያከናውነው ብሔራዊ የጥራት ሽልማት መርሐ ግብር ለሀገራዊ ግባችን ስኬት ትልቅ አቅም የሚፈጥርና የሚበረታታ ነው ብለዋል።