ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢትዮጵያን ታላቁን የክብር ኒሻን ለቢል ጌትስ ዛሬ ማምሻውን በብሔራዊ ቤተመንግሥት በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት ሸልመዋል።
ይኽ የከበረ ሽልማት የጌትስ ፋውንዴሽን ባለፉት 25 አመታት በኢትዮጵያ ላበረከታቸው አሻጋሪ ሥራዎች እና ታላላቅ ዘመን ተሻጋሪ በጎ ተፅዕኖዎችን ያከበረ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በንግግራቸው ለቢል ጌትስ ፋውንዴሽን የ25 አመታት አሸጋጋሪ ሥራዎች ምስጋና አቅርበዋል።
ቢል ጌትስ ከቴክኖሎጂ ፈር ቀዳጅነት ወደ በጎ አድራጊነት ያደረጉትን ጉዞ በማውሳትም ዝቅ ብሎበማገልገል፣ በአክብሮት እና በእኩልነት እምነት ላይ የተመሠረተውን አገልግሎታቸውን አድንቀዋል።

ፋውንዴሽኑ በጤና፣ ግብርና፣ዲጂታል መታወቂያ የሚያደርገው ጥረት ብሎም ጠንካራው በመከባበር ላይ የተመሠረተ ትብብር በጠቅላይ ሚኒስትሩ መወሳቱን ጽህፈት ቤቱ በመረጃው አመልክቷል።