በጽናት የመስራት፣ በማሳ የመተጋገዝ ባህል በሁሉም አካባቢ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገልፀዋል።
በጅማ ዞን ሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ የሻይ ቅጠል ልማትን መጎብኘታቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናግረዋል።
የአካባቢን ጸጋ ለይቶ ከራስ የተሻገረ፤ ሀገርን በሚጠቅም ትጋትና ቁርጠኝነት በልማት መገኘት እያመጣ ያለውን ውጤት በተጨባጭ እየታዬ ነው ብለዋል።
በጉብኝታችን የገጠር አካባቢን ምቹ እና እያዘመነ የሚገኘውን ኮሪደር ልማት ተምሳሌት የሚሆን ስራ ተመልክተናል። በጽናት የመስራት፣ በማሳ የመተጋገዝ ባህል በሁሉም አካባቢ አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።
አካባቢው የሚታወቅበትን የሻይ ቅጠል ልማት የሚያበረታታ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በጅማ ዞን ሰቃ ጮቆርሳ ወረዳ ከነዋሪዎች ጋር በጋራ ማከናወናቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አጋርተዋል።