ፑቲን ለሰላም ድርድር ከዘለንስኪ ጋር ለመገናኘት ዝግጁነታቸውን አስታወቁ

You are currently viewing ፑቲን ለሰላም ድርድር ከዘለንስኪ ጋር ለመገናኘት ዝግጁነታቸውን አስታወቁ

AMN – ሰኔ 12/2017 ዓ.ም

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለሶስት ዓመት የዘለቀውን የሩሲያ እና ዩክሬን ግጭት ለማስቆም በሚደረገው ድርድር የመጨረሻ ምዕራፍ ከዩክሬን አቻቸው ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ለመገናኘት ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ።

ፑቲን አሁን ያለውን ግጭት ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱም ሊፈጠሩ የሚችሉ ግጭቶችን መከላከያ መንገዶችን መፍጠር አለብን ያሉ ሲሆን የመጨረሻው ድርድር የግጭቱ ማብቂያ መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ዘለንስኪ በሃገሪቱ ወታደራዊ አገዛዝ ስር ያለው የ5 ዓመት የስልጣን ዘመኑ በማብቃቱ የሰላም ድርድር የመፈራረም መብት የለውም ሲሉ ፑቲን መናገራቸውን አር ቲ ኢ ዘግቧል።

የሩሲያው ፕሬዝደንት የዩክሬን አቻቸውን በአካል ለማግኘት ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቆየታቸውን ተከትሎ የሃገራቱን ግጭትን ለማስቆም የተደረጉ ድርድሮች እስካሁን ከፍተኛ ውጤት አለማስገኘታቸው ይታወሳል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review