የዘንድሮዉ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከአምናው የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing የዘንድሮዉ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከአምናው የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑ ተገለጸ

AMN ሰኔ 17/2017 ዓ.ም

የዘንድሮዉ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከአምናው የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አጠቃላይ ካውንስል አባላት የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50% እንዲሆን ወስነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በከተማ አስተዳደሩ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በየአመቱ መሻሻል እያሳየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራቱ በዘንድሮዉ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከአምናው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በ2017 ዓ.ም የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርትን ለማሻሻል ተግባራዊ የተደረገው ስትራቴጂም በተማሪዎች ውጤት መረጋገጡን ጠቁመዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አበበ ቸርነት ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ እንደተናገሩት የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዉጤት ዛሬ ከሰአት በኋላ ይፋ ይደረጋል፡፡

በቀጣይ ጥቂት ቀናትም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ውጤት ይፋ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩ በ2017 ዓ.ም 70,525 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መውሰዳቸውን ገልጸዋል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review