የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፕሮጀክቶችን ከመጀመር ባለፈ በጥራትና በፍጥነት አጠናቆ ለሚፈለገው ዓላማ ማዋል ከመቼውም ጊዜ በላይ ባህል እየሆነ መምጣቱን ገለጹ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ የሁለተኛው ዙር ኮሪደር ልማት አካል የሆነው ከ4 ኪሎ እስከ እንጦጦ ኮሪደር ፕሮጀክቶች ተመርቀዉ ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸዉን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ገልጸዋል፡፡
ፕሮጀክቶችን ከመጀመር ባለፈ በጥራትና በፍጥነት አጠናቆ ለሚፈለገው ዓላማ ማዋል ከመቼውም ጊዜ በላይ ባህላችን እየሆነ መምጣቱ ዛሬ የምናስመርቃቸው 4 ኪሎ እስክ እንጦጦ ኮሪደር እውነተኛ ማሳያ ናቸው፡፡
በአገራችን ዘመናዊ የአገር ግንባታ ሂደት ከፍተኛ ሚና ያላቸው ተቋማት መገኛ ፣ የህዝብ እንደራሴዎች መቀመጫ ፣ የምሁራን አምባ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መገኛ ፣ በአገሪቱ የመጀመሪያው የህክምና ተቋም የካቲት 12 ዘመናዊ ሆስፒታል መገኛ ፣ የመጀመሪያው የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት ሙዚየሞችና የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማትና እንዲሁም የከተማችን የእደ ጥበብ ውጤቶች ልህቀት ማዕከል የሆነው ሽሮሜዳ መገኛ ፤ በአጠቃላይ በርካታ ግዙፍ መንግስታዊና ታሪካዊ ተቋማት የሚገኙበት መስመር የሚሸፍነው እና 314 ሄክታር ስፋት ያለው መሬት የለማ ሲሆን ::
ይህ ኮሪደር ልማት በፊት ከነበረው 32 ሜትር ስፍት ወደ 42 ሜትር የመንገድ የስፋው ፤ 3 ሜትር የብስከሌት መንገድ እንዲሁም 11 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ጨምሮ 11 የታክሲ እና የአውቶቡስ መጫኛና ማውረጃዎች ተሰርተውለታል።

ከዚህ በተጨማሪ 20 አረንጓዴ ቦታዎችና 2 ፕላዛዎች እንዲሁም 10 የህጻናት የመጫዎቻ እና 7 የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎችን ጨምሮ 9 መጸዳጃ ቤቶች ፣ ከ5 – 13 ሜትር ስፋት ያለው 11.4 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ፣ 2 (1 ዘመናዊ ሞልን ያካተተ በመንግስትና የግል አጋርነት እየተገነባ ያለ ተርሚናሎች እና 11 የታክሲ/ባስ መጫኛና ማውረጃዎች ያሉት እንዲሁም 7 የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች እና 417 ስማርት ፖሎች አካቷል።
ይህንን መስመር መልሶ ማልማት፤ማደሰና ማስዋብ ለአገራችንና ለህዝባችን ታሪክ ያለንን ክብር የሚገልፅ ከመሆኑም በተጨማሪ ከ15 ሺ ለሚበልጡ ዜጎች ጊዚያዊ እና ቋሚ የስራ እድል ለመፍጠር ችለናል፡፡
በፊት የነበረው 751 ሱቆች ሲሆኑ በአዲስ የተሰሩ 770 ሱቆች በመጨመር 1521 ሱቆች በዚህ ኮሪደር የኢኮኖሚ ልማት እና የንግድ ልውውጥ እንዲያድግ አድርጓል።
በመጨረሻም ለፕሮጅክቶች ስኬትና በዚህ ደረጃ ዕውን መሆን ቀን ከሌሊት የደከማችሁ ብሎም በተለያየ መንገድ የላቀ አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ አመሰግናለሁ ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡