ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሜሪካ የሚገኘው “ሄኖክ አርጋው ፋውንዴሽን ”ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ 133 አይነት የተለያዩ የህክምና ግብአቶችን ማበርከቱን ገለጹ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሜሪካ የሚገኘው “ሄኖክ አርጋው ፋውንዴሽን ”ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ 133 አይነት የተለያዩ የህክምና ግብአቶችን ማበርከቱን ገለጹ

AMN ነሃሴ 5/2017

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሜሪካ የሚገኘው “ሄኖክ አርጋው ፋውንዴሽን”ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ 133 አይነት የተለያዩ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን እና የህክምና ግብአቶችን ማበርከቱን ገልጸዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት “ቸር ልብ ያላቸው እልፍ ዜጎች አሉን” ፤ ከዲያስፓራ እስከ ሀገር ቤት ካላቸው የሚያካፍሉ፣ ከጎዶሎአቸው የሚሰጡ ፣ በመስጠት ውስጥ ያለን በረከት የተረዱ ፣ ለሀገሬ ምን አደረኩላት የሚሉ፣ ቸር፣ ሀብታም ልብ ያላቸዉ እልፍ ወንድም እህቶች አሉን ።

ዛሬም በሀገረ አሜሪካ ኮሎራዶ ግዛት የሚገኘው “ሄኖክ አርጋው ፋውንዴሽን” ዋጋቸው ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ 133 አይነት የተለያዩ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን እና የህክምና ግብአቶችን አበርክቶልናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

መሳሪያዎቹ ለኩላሊት፣ ለተኝቶ ታካሚዎች፣ ለፅኑ እና መደበኛ ሕሙማን ህክምና ግልጋሎት የሚያግዙ ናቸው።

ሄኖክ አርጋው ፋውንዴሽንን በከተማ አስተዳደሩ፣ በተጠቃሚው ማህበረሰብ እና በራሴ ስም እጅግ አድርጌ እያመሰገንኩ፤ ድጋፉ ለታለመለት ዓላማ እንዲውልም ለአስተዳደሩ የጤና ቢሮ አስረክበናል ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review