AMN ሰኔ 17/ 2018 ዓ.ም

መንግሥት ባደረገው ጥረት በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው ኢትዮጵያውያን መካከል 320ዎቹ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።

ተመላሾች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪያድ የሚገኘውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚሲዮን እና ጂዳ የሚገኘውን ቆንስላ ጽ/ቤት በማስተባበር ባደረገው የዲፕሎማሲ ጥረት በሳዑዲ አረቢያ ለእስር ተዳርገው የነበሩ 1ሺህ 655 ዜጎቻችን የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ እንዲሰጣቸው ተደርጓል።

ይህ ውጤት መንግሥት በውጭ ግንኙነቱ ለዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በሰጠው ትኩረት የተገኘ መሆኑን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
መንግሥት ሕብረተሰቡ ከሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በማኅበራዊ ሚዲያ የታጀበ ሀሰተኛ ማታለያ ድርጊት የውጭ አገር ጉዞ ራሱን እንዲጠብቅ ያሳሰበ ሲሆን ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን የሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታዉቋል፡፡