መደመር ተብሎ የተጀመረው የሀገራዊ ዕሳቤ ጉዞ ዛሬ የመደመር መንግሥት ላይ መድረሱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ

You are currently viewing መደመር ተብሎ የተጀመረው የሀገራዊ ዕሳቤ ጉዞ ዛሬ የመደመር መንግሥት ላይ መድረሱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ
  • Post category:ፖለቲካ

AMN መስከረም 6/2018

መደመር ተብሎ የተጀመረው የሀገራዊ ዕሳቤ ጉዞ ዛሬ የመደመር መንግሥት ላይ ደርሷል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው ‘የመደመር መንግሥት’ የተሰኘው መጽሐፍ በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡

በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ መደመር ተብሎ የተጀመረው የሀገራዊ ዕሳቤ ጉዞ ዛሬ የመደመር መንግሥት ላይ ደርሷል ሲሉም ገልጸዋል።

በአንድ በኩል እየመሩ፣ እየሠሩ፤ በሌላ በኩል እያጠኑ፣ እየመረመሩ ላበረከቱልን መጽሐፍ እናመሰግናለን ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review