የሕዳሴ ግድብ የተጠናቀቀው ተባብረው በሰሩ ክንዶች፤ በብስለት በተመሩ የዲፕሎማሲ ሥራዎች፤ በተደመረ የሀገር ሃብት እና ትውልዳዊ ኃላፊነት መሆኑን አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ

You are currently viewing የሕዳሴ ግድብ የተጠናቀቀው ተባብረው በሰሩ ክንዶች፤ በብስለት በተመሩ የዲፕሎማሲ ሥራዎች፤ በተደመረ የሀገር ሃብት እና ትውልዳዊ ኃላፊነት መሆኑን አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ

AMN መስከረም 10/2018

የሕዳሴ ግድብ የተጠናቀቀው ተባብረው በሰሩ ክንዶች፤ በብስለት በተመሩ የዲፕሎማሲ ሥራዎች፤ በተደመረ የሀገር ሃብት እና ትውልዳዊ ኃላፊነት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የታታሪ ሕዝቦች አምባ፣ የእንቁ ባህላዊ እሴቶች መገኛ፣ የበርበሬ አምራቾቹ እና የእንሰት ወዳጆቹ ምድር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሕዳሴ መጠናቀቅ የልማት ሰንደቁን በድል አውለብልቧል ብለዋል ።

የሕዳሴ ግድብ የተጠናቀቀው ተባብረው በሰሩ ክንዶች፤ በብስለት በተመሩ የዲፕሎማሲ ሥራዎች፤ በተደመረ የሀገር ሃብት እና ትውልዳዊ ኃላፊነት መሆኑንም ገልጸዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ዛሬ የተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ክልሉ የእስከዛሬ ስኬቶችን እሴት በማድረግ ለታላላቅ ሀገራዊ የልማት ግቦቻችን ያለውን መሻት ያሳየ ነው ብለዋል።

ለኢትዮጵያ ልዕልና ከላብ እስከ ደም ጠብታ የመታገል እንዲሁም ሀገር በምትፈልገን በሁሉም የልማት ሰልፎች ፊት ቀድሞ የመገኘት የጋራ አቋምን ዛሬ በድጋፍ ሰልፉ አይተናል ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የሕዳሴን ድል መርህ እና አርዓያ ያደረገ ልማት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀጣይ ይጠበቃልም ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review