በምርጫው ሂደት የሚዲያ ተቋማት ጉልህ ሚና እንደተጫወቱ ተገለጸ

AMN – ሰኔ 9/2018 ዓ.ም

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት የሚዲያ ተቋማት ግልጽነትን፣ የዜጎችን ግንዛቤን እና ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎን ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንደተጫወቱ ተገለጸ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በተመለከተ ከሚዲያ ተቋማ ጋር ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናታለም መለሰን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች፣ የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት አመራሮችና ጋዜጠኞች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ውስጥ የሚዲያ ተቋማት ግልጽነትን፣ የዜጎችን ግንዛቤን እና ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎን ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንደተጫወቱ ተገልጿል፡፡

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ፤ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ኢትዮጵያውያን ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ያሳዩትን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

በምርጫው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ መሳተፉን በመግለጽ ህዝቡ ድምጹን ለመስጠት እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ጸንቶ የዜግነት ኃላፊነቱን እንደተወጣም አንስተዋል፡፡

ሚኒስትሯ አክለውም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት ያንጸባረቀበት መሆኑን ተናግረዋል።

መራጮች በምርጫው ሂደት ያሳዩት ቁርጠኝነት የኢትዮጵያን ሥልጣኔ እና ብሔራዊ አንድነትንም ያሳየ ነው ብለዋል፡፡

በወቅቱ የሚዲያ ተቋማት በምርጫ ጣቢያ ክልሎች ተገኝተው ስለ ምርጫው ሂደት ዘገባ በመሥራት ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦም ምስጋና አቅርበዋል።

ሚዲያዎች ለሕዝቡ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ በማቅረብ የምርጫው ሂደት ግልጽ እና ተዓማኒ እንዲሆን የድርሻቸውን እንደተወጡ ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

የሻምበል ምህረት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review