እንደ ሀገር በአጭር ጊዜ ከተሰሩ ስራዎች የተማርነው ይቻላልን ነው

You are currently viewing እንደ ሀገር በአጭር ጊዜ ከተሰሩ ስራዎች የተማርነው ይቻላልን ነው

‎AMN- ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም

‎እንደ ሀገር በአጭር ጊዜ ከተሰሩ ስራዎች የተማርነው ይቻላልን ነው ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕለ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ገለፁ።

‎ከማለዳው ጀምሮ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ የተለያዩ የልማት ስራዎች ጉብኝት አድርገዋል፡፡

‎በጉብኝቱ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ፣ በአዲስ አበባ ቱሪዝምን መሰረት ያደረጉ የልማት ስራዎች መጎብኘታቸውን ተናግረዋል።

‎በከተማዋ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ ማሳየቷን የገለፁት ርዕሰ መስተዳደሩ፣ ይህ መሆኑ የብልፅግና ፓርቲ አዲስ እሳቤ ይዞ ከመስራቱም ባሻገር፣ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የመጨረስ ባህል መዳበሩን እንደሚያሳይም አመላክተዋል።

‎እንደ ሀገር በአጭር ጊዜ ከተሰሩ ስራዎች የተማርነው ይቻላልን ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ፣ በዚህ ፍጥነት የታየው ኢትዮጰያ እምቅ ሀብት እና አቅም እንዳላት ነው ብለዋል።

‎በተለይም ለተመዘገበው ልማት መፍጠር እና የመፍጠን እሳቤ በፓርቲው መተግበሩ በከተማዋ የተመዘገቡት ስኬቶች ማሳያ እንደሆነ ገልጸዋል።

‎በአሁኑ ጊዜ ካልፈጠርን እና ካልፈጠንን ያደጉ ሀገሮች የደረሱበት ደረጃ መድረስ እንደማይቻል በመግለፅ፣ ከዚህ ቀደም ፕሮጀክቶች በሚሰሩበት ፍጥነት ሀገር ለመለወጥ እሳቤን መቀየር ማስፈለጉን አመላክተዋል።

‎የአዲስ አበባ መለወጥ የሚያሳየው፣ የብልፅግና ፓርቲ በአዲስ እሳቤ ኢትዮጰያን ምን ያህል እየለወጠ መሆኑንም ነው ብለዋል።

‎በዛሬው እለት በመዲናዋ የጎበኘነው የልማት ስራ በእጅጉ የሚያኮራ ነው ያሉት አቶ ሙስጠፌ፣ በሶማሌ ክልል የኮሪደር ልማት ሲሰራ ከአዲስ አበባ ብዙ ልምድ እና ተሞክሮ መወሰዱን ጠቀሰዋል።

‎በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review