ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከማሌዥያ ፌዴሬሽን ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም ጋር ትብብራችንን የበለጠ ለማጠናከር እና ለማስፋት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት አረጋግጠናል ሲሉ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዉ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ባለፈው ዓመት ወደ ማሌዥያ ኦፊሴላዊ ጉብኝት ካደረኩኝ አንድ ዓመት በኋላ፣ የማሌዥያ ፌዴሬሽን ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂምን በኢትዮጵያ ተቀብያለሁ ብለዋል።
ይህ የጉብኝት ልውውጥ ጥልቅ አጋርነታችንን የሚመሰክር ሲሆን ይህም በርካታ ቁልፍ ሰነዶችን በመፈረም ተጠናክሯል።
የመግባቢያ ሰነዶቹ በቱሪዝም፣ በጤና፣ በአየር ትራንስፖርት አገልግሎት፣ በኳላ ላምፑር ከተማ ምክር ቤት እና በአዲስ አበባ አስተዳደር የትብብር መስክ ላይ ያተኮሩ ናቸው::
ባደረግነው የሁለትዮሽ ውይይት፣ ትብብራችንን የበለጠ ለማጠናከር እና ለማስፋት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት አረጋግጠናል ሲሉ ገልጸዋል።