ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአትሌት አበበ ቢቂላ ድል እና የአደባባይ ስፖርታዊ ክንውን የሆነው “ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ” የዓለም አትሌቲክስ ቅርስነት እውቅናን መቀበላቸዉ በስፖርቱ ዘርፍ የሃገሪቱን ብሎም የመዲናዋን ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የሚያጎላ መሆኑን ገለጹ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአትሌት አበበ ቢቂላ ድል እና የአደባባይ ስፖርታዊ ክንውን የሆነው “ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ” የዓለም አትሌቲክስ ቅርስነት እውቅናን መቀበላቸዉ በስፖርቱ ዘርፍ የሃገሪቱን ብሎም የመዲናዋን ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የሚያጎላ መሆኑን ገለጹ

AMN ህዳር 11/2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት የአትሌት አበበ ቢቂላ ድል እና ላለፉት 25 ዓመታት የመዲናችን ብሎም የኢትዮጵያ መገለጫና ተናፋቂ የአደባባይ ስፖርታዊ ክንውን የሆነው “ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ” የዓለም አትሌቲክስ ቅርስነት እውቅናን ተቀብለዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ሩጫ በኢትዮጵያ ትልቅ ታሪክና ቦታ አለው። ላለፉት 65 ዓመታት ኢትዮጵያ በርካታ የረጅም ርቀት ሯጮችን ለዓለም አበርክታለች። አበበ ቢቂላ በ1952 ዓ.ም በጣሊያን መዲና ሮም በተካሄደው 17ኛው የኦሊምፒክ ማራቶን ውድድር ላይ በባዶ እግሩ በመሮጥ እና የወርቅ ሜዳሊያን በማግኘት ታሪካዊ ድል ማስመዝገቡን በመከተል በተለያዩ ወቅቶች የተለያዩ ጀግና አትሌቶች የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓለማ በዓለም መድረክ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ አድርገዋል።

የአትሌት አበበ ቢቂላ ድል እና ላለፉት 25 ዓመታት የመዲናችን ብሎም የኢትዮጵያ መገለጫና ተናፋቂ የአደባባይ ስፖርታዊ ክንውን የሆነው “ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ” የዓለም አትሌቲክስ ቅርስነት እውቅናን ተቀብለዋል።

ይህ እውቅና በስፖርቱ ዘርፍ የሀገራችንን ብሎም የከተማችንን ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የሚያጎላ ነው ብለዋል፡፡

ጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላን፣ የታላቁ ሩጫ ውድድር መስራች የሆነውን ጀግናው አትሌታችን ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴን እና ይህን ውድድር ባለፉት ዓመታት ባማረ ሁኔታ ሲያካሂዱ የቆዩትን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ማመስገን እወዳለሁ።

በቀጣይም ውድድሩን ከዚህም በበለጠ ለማሳደግ እና ብዙ የውጭ ሀገር ተሳታፊዎችን ወደ ከተማችን እንዲያመጣ ለማድረግ የበለጠ ተባብረን የምንሰራ ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

#አዲስሚዲያኔትዎርክ

#Ethiopia

#addisababa

#athletics

#ethiopiangreatrun

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review