ስኬት ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አጠቃላይ የካፒታል መጠኑ 9 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታወቀ።
ባንኩ 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ህዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም አካሂዷል።
የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጥላሁን ወርቁ ስኬት ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አጠቃላይ የካፒታል መጠኑ 9 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር መድረሱን ተናግረዋል።
የባንኩ የተከፈለ የካፒታል መጠን ከ6 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ወደ 7 ነጥብ 84 ቢሊዮን ብር ማደጉን እንዲሁም ጠቅላላ የደንበኞች ቁጥር 615 ሺህ ማድረስ መቻሉን ለጉባዔው ላይ ባቀረቡት አመታዊ የስራ ሪፖርት አንስተዋል።
ስኬት ባንክ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 1 ነጥብ 24 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡንም ባንኩ ለኤኤምኤን በላከው መረጃ አስታዉቋል።