በኦንላይን የተገዛ እቃን እንዴት መመለስ ይቻላል ?

You are currently viewing በኦንላይን የተገዛ እቃን እንዴት መመለስ ይቻላል ?

AMN ህዳር 23/2018

በኤሌክትሮኒክስ ግብይት ተሳታፊዎች መሀከል ፍትሀዊነትን ፣ ደህንነትና መተማመንን ለማስፈን ከ6 አመታት በፊት የኤሌክትሮኒክስ ትራንዛክሽን አዋጅ ቁጥር 1205 /2012 ተደንግጓል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ኤፍ ኤም 96 .3 ራዲዮ መረጃ የሰጡት ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ አቶ ፍቃዱ አንዳርጌ ከሸማቾች ህግ ጥበቃ ጋር በተያያዘ በወጣው አዋጅ ቁጥር 813/2006 አንድ ሸማች የገዛው እቃ ጉድለት ካለበት በ15 ቀናት ውስጥ መመለስ እንደሚችል መቀመጡን አስታውሰዋል ፡፡

ይህንኑ ህግ የሚያግዘው ከዲጂታል ግብይት ጋር በተገናኘ የኤሌክትሮኒክስ ትራንዛክሽን አዋጅ ቁጥር 1205/2012 ደግሞ በዲጂታል መንገድ ወይም ኦንላይ በሚደረጉ ግብይቶች ሸማቹ የገዛውን እቃ ጉድለት ኖሮበት ይሁን ጉድለት ሳይኖርበት በ7 ቀናት ውስጥ መመለስ እንደሚችል ያሳያል ብለዋል ፡፡

በኦንላይን ግብይት የተገዛው እቃ ሲመለስ የተገዛው እቃ በሸማቹ እጅ ሲቆይ ለብልሽት የሚዳረግ መሆን አለመሆኑ ፤ የትራንስፖርት ወጪና ሌሎች አንዳንድ ጉዳዮች ታሳቢ ሊደረጉ እንደሚገባም አቶ ፍቃዱ አስገንዝበዋል ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በኦን ላይን ምርት የሚያቀርቡ ግለሰቦችም ይሁኑ ተቋማት የተሟላ አድራሻቸውን፣ ስለሚያቀርቡት ግብይት፣ ምርት እና አገልግሎት፣ ግብይቱ ስለሚፈጸምበት መንገድ የመሳሰሉ የግብይት መረጃዎችን ለሸማቹ የማቅረብ እና ግብይቱን በሚያከናውኑበት ፕላትፎርም ላይ የማስቀመጥ ግዴታ እንዳለባቸው ተደንግጓል ብለዋል ፡፡

ሽመልስ ታደሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review