ብሪክስ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚና ዲፕሎማሲ ዕድገት አዳዲስ እድሎችን የሚያሰፋ ነው

You are currently viewing ብሪክስ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚና ዲፕሎማሲ ዕድገት አዳዲስ እድሎችን የሚያሰፋ ነው

AMN- መስከረም 4/2019 ዓ.ም

ብሪክስ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተደማጭነት ለማጠናከር የተቋቋመ ዓለም አቀፍ ጥምረት ነው።

የምዕራባውያንን የኢኮኖሚ የበላይነት ሚዛናዊ ለማድረግ እና ፍትሃዊ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ሥርዓት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሰው ይህ ጥምረት ለኢትዮጵያ ሁለገብ ዕድገት ሚናው የላቀ ነው።

ኢትዮጵያ የዚህ ስብስብ አካል መሆን መቻሏ ለአገሪቱ የውጭ ግንኙነት እና የኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

አሁን ላይ ጥምረቱ በግዥ አቅም የዓለምን 35 በመቶ ጠቅላላ የውስጥ ምርት (GDP) የሚሸፍኑ 11 ሀገራትን አቅፎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ኅብረቱ የፋይናንስ ነፃነትን እና የልማት አማራጮችን ከማስፋት አንፃር ለአባል ሀገራቱ ትልቅ አቅም ይፈጥራል።

ከዚህም ባለፈ ኢትዮጵያ ከቻይና፣ ከሕንድ እና ከብራዚል ጋር ጠንካራ የንግድ ግንኙነት በመፍጠር ቡና እና የቅባት እህሎችን የመሳሰሉ የግብርና ምርቶችን ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ማድረስ ተችሏል።

ዓለም አቀፍ የንግድ ልውውጡ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ወደ ሀገሪቱ እንዲፈስ በማድረግ የማኑፋክቸሪንግ፣ የቴክኖሎጂ እና የኢንዱስትሪ ልማትን እያፋጠነው ይገኛል።

በአፍሪካ ቀንድ ስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ የዚህ ኅብረት አባል መሆኗ፤ የራሷን የልማት አጀንዳዎች ከማስጠበቅ ባለፈ የምሥራቅ አፍሪካን ፍላጎት በዓለም አቀፍ መድረክ ለማንጸባረቅ ያስቻላት ነው።

ከቻይና፣ ሕንድ እና ሩሲያ ካሉ ሀገራት የቴክኖሎጂ፣ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና የግብርና ዘመናዊ አሠራር ልምዶችን በመቅሰም ሀገራዊ አቅምን ማሳደግ ተችሏል።

ዘንድሮም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕንድ ኒው ዴልሂ በተካሄደው 18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ፣ ፍትሃዊ የሆነ ዓለም አቀፍ ሥርዓት እንዲገነባ ማገዝና የኢኮኖሚ ዕድሎችን ማስፋት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ አባል ሀገራቱ ከመቸውም ጊዜ በላይ ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ መግለፃቸው የሚታወስ ነው።

በበረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review