የዘመን መለወጫ በዓል ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር ፋይዳው የጐላ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing የዘመን መለወጫ በዓል ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር ፋይዳው የጐላ መሆኑ ተገለጸ

AMN- መስከረም 4/2019 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የዘመን አቆጣጠር ልዩነትንና የነፃነት ታሪክን ከማብሰር ባለፈ፣ ዜጎች ከልዩነት ወጥተው በጋራ የሚቆሙበት፣ ፍቅርና መተሳሰብን የሚያጠናክሩበት እንዲሁም ሀገራዊ ሉዓላዊነትን የሚያስቀጥሉበት ታላቅ በዓል መሆኑን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ።

አምባሳደር ዲና ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት ልዩ ባህሪያትና ማህበራዊ እሴቶችን አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃ የቆየች፣ የራሷ ፊደል እና የዘመን አቆጣጠር ያላት ሀገር መሆኗን የገለጹት አምባሳደሩ፣ ይህ እውነታ ሀገሪቱን በዓለም አቀፍ ደረጃ ልዩ እንደሚያደርጋት አንስተዋል።

አዲስ ዓመት ከማንኛውም ብሔር እና ማህበራዊ መዋቅር ውጪ የህዝብ አንድነት የሚገለጽበት፣ የህዝቡ ስነ-ልቦናዊ ውቅር በአንድነት የሚጠናከርበት መሆኑንም አምባሳደር ዲና ጠቁመዋል።

በዓሉ ፍቅርን፣ መተሳሰብን እና መረዳዳትን የሚያስተመር በመሆኑ ለሀገር ገጽታ ግንባታና ለሉዓላዊነትን ለማስቀጠል ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገልም አሳስበዋል።

በሌላ በኩል የባህልና ስነ-ልቦና ጥናት ተመራማሪው አቶ እድሜአለም ግዛው በሰጡት አስተያየት፣ መስከረም ለአዲስ ተስፋ መጀመሪያ የሚሆን የብርሃን ማንጸባረቂያ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያውያን ስነ-ልቦና ከምዕራባውያን በተለየ መልኩ ከእምነት፣ ከልብ ንጽህና እና ከእሴቶች ጋር የተቆራኘ መሆኑን አንስተዋል።

በዓሉ ይቅርታን፣ አብሮ መብላትን፣ ፍቅርንና መራራትን በማጠናከር እውነተኛ የውስጥ ለውጥ የሚመጣበት ትልቅ እሴት መሆኑንም ተመራማሪው አብራርተዋል።

በፍሬህይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review