ማንችስተር ሲቲ ከፉልሃም ጋር ያደረገውን የ14ኛ ሳምንት መርሃግብር ጨዋታ አሸንፏል። አስገራሚ ድራማ የታየበት ጨዋታ በሲቲ 5ለ4 አሸናፊነት ተጠናቋል።
ማንችስተር ሲቲ በፊል ፎደን ሁለት ፣ ኧርሊንግ ሃላንድ ፣ ቲጃኒ ራይንደርስ እንዲሁም ሳንደር በርግ በራሱ ላይ ባስቆጠሯቸው ግቦች 5ለ1 የመምራት እድል አግኝቶ ነበር።
ጨዋታው ግን በዚህ የሰፋ የግብ ልዩነት አልተጠናቀቀም። ቀድሞ ኤሚል ስሚዝ ሮው ካስቆጠረው ግብ በተጨማሪ ፣ ሳሙኤል ቺክዌዜ ሁለት ፣ አሌክስ ኢዎቤ ሌላ ግብ አክሎ ጨዋታው 5ለ4 ተጠናቋል።
በጨዋታው ግብ ያስቆጠረው ኧርሊንግ ሃላንድ በሊጉ 100ኛው ሆኖ ተመዝግቧል። አጥቂው ግቦቹን ያስቆጠረው 111 ጨዋታ አከናውኖ ነው።
በዚህም ባነሱ ጨዋታዎች 100 ግብ ላይ የደረሰ ቀዳሚው ተጫዋች መሆን ችሏል። የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን ከመሪው አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት አጥቧል።
አርሰናል ነገ ከብሬንትፎርድ ጋር የሚጫወት ይሆናል። ሲቲ ምንም እንኳን ነጥቡን ያጥብ እንጂ ጨዋታዎችን የሚያሸንፍበት መንገድ አሳማኝ አልሆነም።
በሌላ ጨዋታ ኤቨርተን ከሜዳው ውጪ በጃክ ግሪሊሽ ግብ ቦርንማውዝን 1ለ0 አሸንፏል።
በሸዋንግዛው ግርማ