የኢትዮጵያ የሙያ ማሕበራት ተሳትፎ ለሀገራዊ ምክክር ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለፀ

You are currently viewing የኢትዮጵያ የሙያ ማሕበራት ተሳትፎ ለሀገራዊ ምክክር ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለፀ

AMN-ህዳር 25/2018

የሙያ ማሕበራት የላቀ ተሳትፎ ለሀገራዊ ምክክር ውጤታማነት በሚል መሪ ሀሳብ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕሮፌሰር) አሳታፊና አካታች አገራዊ ምክክር በስኬታማነት ለማከናወን የሚያስችሉ መድረኮችን ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር መካሄዳቸውን ገልፀዋል።

ይሕም እንደሀገር ላለመግባባት ምክንያት የሆኑ መሠረታዊ ችግሮችን በመለየት ወደ መድረክ በማምጣት ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር ያስችለናል ሲሉ ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

ዋና ኮሚሽነሩ አያይዘውም ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት የሙያ ማህበራት የላቀ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አንስተው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ብቸኛ መፍትሄ የሆነውን ምክክር በስኬት ለማጠናቀቅ ከሙያ ማህበራቱ ጋር ተቀራርቦ መስራት አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።

ኮሚሽኑ ባለፍት ሶስት አመታት ያከናወናቸው ዋና ዋና ክንውኖችና ቀሪ ስራዎቹን እንዲሁም እስካሁን ያጋጠሙትን ተግዳሮቶችና ችግሮችን ለመፍታት ያደረገውን ጥረት እና የሙያ ማሕበራት ተሳትፎ እና ሚና ምን ሊሆን ይገባል የሚሉ ሀሳቦች በመድረኩ ላይ ቀርበዋል።

በምክክር መድረኩ ከተለያዩ ሲቪክ ማሕበረሰብ ድርጅቶችና ሰራተኛ ማህበራት አመራሮችና ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን እንደሀገር ዘላቂ ሰላምን ለመፍጠር ሀገራዊ መግባባት ወሳኝ መሆኑን አንስተው ለስኬቱ በባለቤትነት ባላቸው ሙያና እውቀት ተጠቅመው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በታምሩ ደምሴ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review