የመደመር መንግሥት ሀገር በቀል ፍልስፍና ከኢትዮጵያውያን እሴቶች ጋር የተጋመደ ነው

You are currently viewing የመደመር መንግሥት ሀገር በቀል ፍልስፍና ከኢትዮጵያውያን እሴቶች ጋር የተጋመደ ነው
  • Post category:ፖለቲካ

AMN፣ ሕዳር 25/2018 ዓ.ም

የአፍሪካ ጉዳዮች ተመራማሪ የሆኑት ዮሴፍ ቤኮ (ዶ/ር) “የመደመር መንግሥት” ፅንሰ-ሀሳብን ከኢትዮጵያውያን አኗኗር፣ ዕምነት፣ ባሕልና እሴቶች ጋር በእጅጉ የተጋመደ መሆኑን ገልጸዋል።

ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር ቆይታ ያደረጉት ተመራማሪው የመደመር አስተሳሰብ እንደ ግራ ወይም ቀኝ ዘመም የዓለም ፖለቲካዊ አሰላለፍ የሚመደብ ሳይሆን ራሱን የቻለ አዲስ (ፍልቀታዊ) እሳቤ መሆኑን አስረድተዋል።

ዶክተር ዮሴፍ እንዳብራሩት የመደመር መንግሥት እሳቤ አዲስ ጽንሰ ሐሳብ አዲስ የሆነበት ምክንያት ከየትኛውም የውጪ ርዕዮት ያልተቀዳና አፍሪካዊ መሠረት ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

የመደመር መንግስት እሳቤ በዓለም ሁኔታ ውስጥ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ድርሻ ምን መሆን እንዳለበት ይመልሳል ያሉት ተመራማሪው በተለይ ከተሜነት የሥልጣኔ መነሻ፣ የቴክኖሎጂ መፍለቂያ እንዲሁም የሀገር ዕድገት መዳረሻ አድርጎ እንደሚያምን ተናግረዋል።

ለዚህ ማሳያ አድርገው ያስቀመጡት ደግሞ በከተሞች በተለይም በአዲስ አበባ የተጀመረውን የለውጥ እና የጽዳት እሳቤ ሲሆን ይህ ስኬት የሌሎች ከተሞችን ትንሳኤ የሚያበስር ይሆናል ብለዋል።

የመደመር መንግሥት ጽንሰ ሐሳብ ኢትዮጵያውያን ችግሮቻቸውን በራሳቸው ሀብት፣ አዲስ አስተሳሰብ እና ቴክኖሎጂ እንዲፈቱ የሚያስችል ተቀባይነት ያለው አዲስ አስተሳሰብ ስለመሆኑ ያላቸውን ዕምነት ገልጸዋል።

‎በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review