በ14ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዌስትሃም ዩናይትድን የገጠመው ማንችስተር ዩናይትድ 1ለ1 ተለያይቷል። ብዙ የግብ እድል ባልተፈጠረበት ጨዋታ ዲያጎ ዳሎ የዩናይትድን ግብ አስቆጥሯል።
ፖርቹጋላዊው ተከላካይ በኦልድትራፎርድ ያስቆጠረው የመጀመሪያ የፕሪምየር ሊግ ግቡ ሆኖ ተመዝግቧል። ለዌስትሃም ሶንጎቶ ማጋሳ የአቻነቷን ግብ ከመረብ አሳርፏል።
ከ14 ጨዋታ 22 ነጥብ የሰበሰበው ዩናይትድ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በሸዋንግዛው ግርማ