በተቀናጀ ሀገር አቀፍ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ 24.8 ሚሊየን ሕጻናት ይከተባሉ

You are currently viewing በተቀናጀ ሀገር አቀፍ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ 24.8 ሚሊየን ሕጻናት ይከተባሉ

AMN- ታህሳስ 3/2018 ዓ.ም

የተቀናጀ ሀገር አቀፍ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ 24.8 ሚሊየን ሕጻናት እንደሚከተቡ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ሀገር አቀፍ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሀዋሳ ከተማ ተካሂዷል።

ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ቀናት በሚሰጠው የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በሀገር አቀፍ ደረጃ 24.8 ሚሊዮን ሕፃናት እንደሚከተቡ በመርሐ-ግብሩ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ገልጸዋል።

‎ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት፣ የክትባት ዘመቻው ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ይሰጣል ብለዋል።

በመሆኑም ወላጆች እና አሳዳጊዎች ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናትን በማስከተብ ከፖሊዮ በሽታ እንዲታደጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ቤት ለቤት እና በትምህርት ቤት ለሚሰጠው የክትባት ዘመቻ ውጤታማነት የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡም ዶክተር መቅደስ አሳስበዋል።

‎እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ፣ በዘመቻው ከፖሊዮ ክትባት ባሻገር የሌሎች ክትባት አይነቶችን የማጠናከር፣ በሽታን የመከላከል እንዲሁም የማህበረሰብ ጤና አጠባበቅ ትምህርት ይሰጣል።

ከክትባቱ ባሻገር ‎የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ቅኝት እንደሚካሄድ ተዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review