ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ “የኢትዮጵያ የክብር ኒሻን” በመሸለማቸዉ የተሰማቸዉን ደስታ ገለጹ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ “የኢትዮጵያ የክብር ኒሻን” በመሸለማቸዉ የተሰማቸዉን ደስታ ገለጹ

AMN ታኅሣስ 8/2018

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ ስብሰባዉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በተገኙበት ዛሬ አካሂዷል፡፡

የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲም በጋራ ስብሰባዉ ላይ ንግግር አድርዋል፡፡

ዛሬ በእናንተ ፊት ቆሜ ንግግር ማድረግ በመቻሌ ከፍተኛ ክብር ይሰማኛል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምድረ ቀደምትና የሰዉ ዘር መገኛ በሆነች ኢትዮጵያ በመገኘቴ ደስተኛ ነኝ ብለዋል፡፡

የትውልድ ግዛቴ የአንበሶች መገኛ በሆነችዉ ጉጃራት ብትሆንም ኢትዮጵያ ስመጣ ወደ ቤቴ የመጣሁ ያህል ደስታ ይሰማኛል ነዉ ያሉት፡፡

ኢትዮጵያ ለጀመረችዉ የዴሞክራሲ ጉዞ እዉቅና የሰጡት የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲም ከ1.4 ቢሊዮን በሚበልጠዉ የሕንድ ሕዝብ ስም የወዳጅነት፣ የመልካም ፈቃድ እና የወንድማማችነት ሰላምታቸዉን አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያ አቻቸዉ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እጅ ‘የኢትዮጵያ ክብር ኒሻን’ በመቀበላቸዉም በህንድ ሕዝብ ስም የተሰማቸዉን ደስታ ገልጸዋል፡፡

ይህንን ሽልማት በታላቅ ትህትና በሕንድ ሕዝብ ስም ተቀብያለሁ አመሰግናለሁ ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review