AMN – ሚያዝያ 8/2018 ዓ/ም
በንፋስ ኃይል አማካኝነት ጨለማን ለመግፈፍ፣ ዐቅምን በለየ የቅድመ ጥናት እና ልዩ እቅድ ወደ ተግባር ዛሬ የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫን እውን አድርጋለች። ይህ ፕሮጀክት 100 ሜጋ ዋት ንጹህ የኃይል አቅርቦት በመጨመር ወደ ዘርፈ ብዙ እና ቀጣይነት ባለው የኃይል መጻዒ ዕጣ ፈንታ ለመገንባት የምናደርገውን ጉዞ ያጠናክረዋል። ይህም አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ለማረጋገጥና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ አብነት ነው።

ለዘመኑ የኃይል ዐቅም ተደማሪ የሆነውን ፕሮጀክት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ተገኝተን በኩራት እያስመረቅን፤ የተገኘው ውጤት መሰል ስራዎችን ለማበራከት የሚያተጋን ነው።
በሁሉም ዘርፎች የምናስመዘግበው የኢትዮጵያ የዕድገት ጉዞ ተጠናክሮ እየቀጠለ፣ ይበልጥም እየለማ ይሄዳል። ከምንጊዜውም በላይ ታላቅ የምንሆንበት ጊዜ ሩቅ አይደለም! – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ( ዶ/ር)