ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጂ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት ለረጅም ጊዜ ለዘለቀው እና ተዐማኝነትን ላተረፈው ትስስር ጉልህ የሆኑ እርምጃዎች ናቸው ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡
ከአስተዳደር እና ከሰላም አጠባበቅ እስከ ዲጂታል አቅም ግንባታ እና ትምህርት ድረስ፣ ትኩረቱ ህዝባችንን በማብቃት ላይ ነው። በእውቀት፣ በክህሎት እና በፈጠራ ላይ ያለው ትኩረት የነገው አንቀሳቃሾች ወጣቶች መሆናቸውን ያለን የጋራ እምነት ያሳያል።
በጤና አጠባበቅ ውስጥ ያለው ትብብር ለሰብአዊ ክብር እና ለተጋላጭ ወገኖች እንክብካቤ ጥልቅ ቁርጠኝነትን ያሳያል።
እነዚህ ውጤቶች የህንድ-ኢትዮጵያ አጋርነት በእድገት እና ሰው-ተኮር የሆኑ ልማቶች ላይ ማተኮራቸውን ያንፀባርቃሉ።

በአድዋ ድል ሐውልት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠናል። ሐውልቱ የኢትዮጵያን ወኔ፣ አንድነት እና የማይናወጥ መንፈስ የሚያሳይ ኃይለኛ ምልክት ነው።
ይህም ሐውልት በቆራጥነት ራሷን ስለጠበቀች ኩሩ ሀገር ዓለምን ያስታውሳል በማለት በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡