በአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ማህበር የሚዘጋጁ ውድድሮች መቀነሳቸዉን ተከትሎ አትሌቶች ያለ እድሜያቸው ወደ ጎዳና ላይ ውድድሮች እያመሩ ነው መሆኑን ከኤኤምኤን ጋር ቆይታ ያደረገዉ ቀነኒሳ በቀለ ተናገረ ፡፡
አትሌቶች ከትራክ ወደ ጎዳና የሚያመዝኑበት ምክንያትም ከውድድር በኋላ ለአትሌቱ የሚሰጠዉ ጥቅም በቂ አለመሆኑን ነው ቀነኒሳ የገለፀው ፡፡
በፊት የነበረዉ ብሄራዊ ቡድን መበተኑም የቡድን መንፈስ ላይ ክፍተት ፈጥሯል የሚለዉ ቀነኒሳ አሰልጣኞች ምክር በመስጠት ሊመልሱት እመንደሚገባም አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
በአልማዝ አዳነ