AMN – ታኅሣሥ 10/2018 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ ከመጡት የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሀሰን ሼኽ ሞሃሙድ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ባለፈው አንድ አመት እየሰራንባቸው የቆየነውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ውይይቶች በመቀጠል ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

የሃሳብ ልውውጣችን የወል የቅድሚያ ጉዳዮቻችንን ለመከወን ብሎም ለጠንካራ ግንኙነት፣ ቀጠናዊ መረጋጋት እና ልማት ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያፀና ነበር ሲሉም አክለዋል።
