በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባትን ለሚያመጡ የተቋማት ግንባታዎች ትኩረት መደረጉን የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባትን ለሚያመጡ የተቋማት ግንባታዎች ትኩረት መደረጉን የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር) ገለጹ

AMN- ጥቅምት 17/2019 ዓ.ም

በመደመር መንግስት የማኅበረሰብ እምነትን ለመገንባት፣ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባትን ለማምጣት የሚያስችሉ የተቋማት ግንባታ እና አሠራሮች ትኩረት እንደተሰጣቸው በሰላም ሚኒስቴር የግጭት አፈታት እና የሰላም ግንባታ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በካናዳ ኢምባሲ ሚኒስትር ካውንስለር እና የትብብር ኃላፊ ሾን ቦይድን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።በውይይታቸውም በሰላም ግንባታ፣ በሀገራዊ ምክክር፣ በአካታችነት እና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በውይይቱ ላይ በመደመር መንግስት ማኅበራዊ አንድነትን፣ ኢኮኖሚያዊ ትስስርንና ዘላቂ ሰላምን ለማጠናከር እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን አንስተው፣ በተለይም ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት፣ የተለያዩ ማኅበረሰቦችን በሀገር ግንባታ ሂደት ለማሳተፍ እና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን ለበርካታ ዘመናት ሲያነሷቸው የቆዩ ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሀገራዊ ምክክር ሂደትን አካታች በሆነ መልኩ መከናወኑን ጠቁመዋል። ተቋማት የአካታችነትን እና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን መርህ ተከትለው እንዲሰሩ እንዲሁም ውጤታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ልምዶች እና የትብብር ዕድሎች እንዲጎለብቱ አድርገዋል ብለዋል።

እነዚህ ተግባራት ዘላቂና አዎንታዊ ሰላምን በመገንባት የኢትዮጵያን ስልጣኔ ለማስቀጠል ጉልህ ሚና እንዳላቸው ገልጸው የካናዳ መንግስትም በኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ እያደረገ ላለው ትብብርም ሚኒስትር ዴኤታው አመስግነዋል።

የካናዳ ኤምባሲ ሚኒስትር ካውንስለር እና የትብብር ኃላፊ ሾን ቦይድ በበኩላቸው፣ የካናዳ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት በማጠናከር፣ የጋራ ጥቅሞችን በሚያሳድጉ የትብብር መስኮች ላይ አብሮ ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

መንግስታቸው ኢትዮጵያ በሰላም ግንባታ፣ በማኅበራዊ ትስስርና በኢኮኖሚ ግንባታ ዙሪያ እያስመዘገበች ያለውን ለውጥ አድንቀው በጋራ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ማሳየታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review