ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነውን የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያ በይፋ መረቁ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነውን የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያ በይፋ መረቁ

AMN- ሰኔ 13/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ‘‘ዲጂታል ለልህቀት’’ በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ በመገኘት፣ ከተለያዩ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በአንድ መድረክ ላይ የሚያጣምረውን እና በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነውን የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያ በይፋ መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ይህ ታላቅ ስኬት ለሀገራችን ከፍተኛ ኩራት ከመሆኑም በላይ በቴክኖሎጂ የሚመራ እና ዓላማ ተኮር ኢንቨስትመንት ምን ሊያስገኝ እንደሚችል ማረጋገጫ ነው ብለዋል፡፡

የኢኮኖሚ ወሳኝ መሠረተ ልማት የሆነው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ የዜጎችን ጊዜ ይቆጥባል፣ የሙስና ቀዳዳዎችን ይደፍናል፣ እንዲሁም በመንግሥት በኩል የተቋማትን ታማኝነትና ጥንካሬ ያጎለብታል ሲሉ ገልጸዋል።

ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያ ትልሞች ተራ ምኞት ሳይሆኑ፣ በራሳችን እጆችና አቅም የምንገነባቸው እውነታዎች መሆናቸውን በግልጽ የሚያሳይ ምስክር ነውም ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህንን ስኬት ይበልጥ በማጠናከር፣ የተገኘውን ልምድና ተሞክሮ ለአፍሪካውያን ወንድሞች እና እህቶች በማካፈል እንዲሁም ከዚህ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት መጓዝ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review