የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችን በልዩ ሁኔታ ተጠቃሚ በሚያደርጉ የስራ ዕድሎች ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችን በልዩ ሁኔታ ተጠቃሚ በሚያደርጉ የስራ ዕድሎች ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ

AMN ታኅሣሥ 11/2018

ወጣቶችን በልዩ ሁኔታ ተጠቃሚ በሚያደርጉ የስራ ዕድሎች ላይ ከተማ አስተዳደሩ እየሰራ እንደሚገኝ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ ገለጹ

ኃላፊው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በስራ ዕድል ፈጠራ እና በመንግስት የድጋፍ ማዕቀፍ ዙሪያ ባዘጋጀው የወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ ነው ይህን የተናገሩት።

አዲስ አበባ ከተማ በከፍተኛ የልማት ሂደት ላይ ትገኛለች ያሉት አቶ ሚሊዮን፤ እነዚህ ልማቶች ከሚፈጥሯቸው የስራ ዕድሎች ውስጥ ወጣቱን በልዩ ሁኔታ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የስራ ዕድል ማዕቀፎችን መንግስት ስለማመቻቸቱ ተናግረዋል።

በእነዚህ የስራ ዕድሎች ተጠቃሚ ለመሆን ታዲያ ወጣቱ ሙሉ ዝግጁነት ሊኖረው እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በተለይም የሚፈጠሩ የስራ ዕድሎችን ሳይመርጡ የመስራት ባህልን ሊያዳብሩ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ በከተማዋ ለሚገኙ 79 ሺህ ወጣቶች የስራ ዕድል መፈጠሩን የተናገሩት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ናቸው።

በዚህም በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ላይ በዕቅድ ከተያዘው አንጻር የ83 በመቶ አፈጻጸም መኖሩን ተናግረዋል።

ከስራ ፈጠራው ጎን ለጎን ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር አገልግሎት መመቻቸቱንም አቶ በላይ ደጀን በመድረኩ አንስተዋል።

በላይሁን ፍስሃ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review