AMN- ነሐሴ 6/2018 ዓ.ም

አዲስ አበባ በደረቅ እና ፈሳሽ ቆሻሻ አስተዳደር የከተማዋን ገጽታ የለወጡ መጠነ ሰፊ ሥራዎችን አከናውናለች።
ከተማ አስተዳደሩ የተገበረው የተቀናጀ የቆሻሻ አስተዳደር ሥርዓት ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ጽዱና ተስማሚ አካባቢን ከመፍጠር ባለፈ የማህበረሰቡ ጤና እንዲጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

ባለፉት አምስት አመታት የዘመነ የቆሻሻ አስተዳደር ስርዓት ተግባራዊ በመደረጉ፣ እጅግ ከፍተኛ ቶን የደረቅ ቆሻሻ እና ፈሳሽ ቆሻሻ በመልሶ መጠቀም ኡደት ውስጥ ውሏል፡፡
የቆሻሻ አስተዳደር ሥርዓቱ ከንጽህና ባሻገር ለከተማዋ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት የማይናቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

በዘርፉ በተደራጁ ወጣቶች፣ ሴቶችና ማህበራት አማካይነት ሰፊ የሥራ እድል ከመፍጠሩም በላይ ቆሻሻን ወደ ሀብት የመቀየር አሰራር ተተግብሯል።
ከዚህ በፊት ለከተማ ብክለትና ለጤና ስጋት የነበረው ቆሻሻ ዛሬ ሃብት እንዲሆን ተደርጓል፡፡
በየዓመቱ በከተማችን ከደረቅ ቆሻሻ በብዙ ቶን ኮምፖስት ለከተማ ግብርና ይመረታል፡፡

እንዲሁም ከደረቅና ፈሻስ ቆሻሻ ለኃይል ማመንጫ መቅረቡ የቆሻሻ አስተዳደር ከመሰብሰብና ከመጣል ወደ ኡደት፣ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እና ኃይል ምንጭነት እየተሸጋገረ ከተማችንን ውብ እና ፅዱ ማድረግ ተችሏል።

ይህ የተቀናጀ የቆሻሻ አስተዳደር ስርዓት አዲስ አበባን ውብ፡ ጽዱ እንድትሆንና ዓለም አቀፍ እውቅናን እንድታገኝ አድርጓታል፡፡
ስኬቱ ከተማዋ ለአገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ጎብኚዎች ሳቢ፣ ምቹና ጽዱ እንድትሆን ያስቻለ ሲሆን ይህም አዲስ አበባን በአፍሪካ ደረጃ ከ10 ጽዱ ከተሞች አንዷ አድርጓታል።
በመሆኑም የጽዳቱ ውጤት አዲስ አበባ የአህጉራችን የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን የሚያረጋግጥ የጽዳትና የመሰረተ ልማት ደረጃ ላይ መድረሷን እንደሚያረጋግጥ ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተገነው መረጃ መለክታል።
See less