በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 17ኛ ሳምንት በሜዳው ቪላ ፓርክ ማንችስተር ዩናይትድን አስተናግዶ 2ለ1 አሸንፏል።
አስደናቂ ጉዞ ላይ የሚገኘው ቪላ ሁለቱን የማሸነፊያ ግቦች በሞሮጋን ሮጀርስ አማካኝነት አግኝቷል። የዩናይትድን ብቸኛ ግብ ማቴኡስ ኩኝሃ ከመረብ አሳርፏል። ቪላ በሁሉም ውድድር 10 ተከታታይ ድል አስመዝግቧል።
ክለቡ ይህን ሲያደርግ 111 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የዛሬው ድል ከመሪው አርሰናል በሦስት ነጥብ ብቻ አንሶ 3ኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ አድርጎታል። በዩናይትድ በኩል አምበሉ ቡርኖ ፈርናንዴዝ ተጎድቶ ተቀይሮ ወጥቷል።
ለጨዋታው ካሲሜሮ በቅጣት እና ኮቢ ማይኑን በጉዳት ያልተጠቀመው ሩበን አሞሪም ጃክ ፍሌቸር እና ሼ ሌሲ ለተሰኙ ታዳጊዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ለዋናው ቡድን እንዲጫወቱ አድርጓል።
በሸዋንግዛው ግርማ