የመሪነት ብቻ ሳይሆን የእናትነት እና የእህትነት እንዲሁም ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑ የተረጋገጠበት ድንቅ ተግባር በአዲስ አበባ

You are currently viewing የመሪነት ብቻ ሳይሆን የእናትነት እና የእህትነት እንዲሁም ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑ የተረጋገጠበት ድንቅ ተግባር በአዲስ አበባ

AMN- ታኅሳስ 16/2018 ዓ.ም

የመሪነት ብቻ ሳይሆን የእናትነት እና የእህትነት እንዲሁም ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑ የተረጋገጠበት ድንቅ ተግባር በአዲስ አበባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትዉልድን መገንባት ሃገርን መገንባት ነው በሚል ፅኑ እምነት ከከተማ ልማት ጎን ለጎን በርካታ ሰዉ ተኮር ስራዎችን በመስራት ዜጎች በሁለተናዊ የልማት ውጤቶች ውስጥ እኩል ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ዕድል መፍጠር ችሏል፡፡

ከእነዚህ በርካታ ሰው ተኮር ስራዎች ዉስጥ በክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሃሳብ አመንጪነት ልበ-ቀና ባለሃብቶችን በማስተባበር ወደ ተግባር የተገባዉ የተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከላት የተጠቃሚ ቁጥሩ እየጨመረ በመምጣቱ በከተማዋ 26 የምገባ ማዕከላት ተገንብተዉ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

በመዲናችን በቀን አንዴ እንኳን መመገብ የማይችሉ፤ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ጧሪ ቀባሪ ያጡ አረጋውያን፣ የአገር ባለውለታዎች፤አቅመ ደካማ ሴቶች እና ህፃናትን በሁሉም የምገባ ማዕከላት በማሰባሰብ በአሁኑ ሰዓት ከ36ሺ በላይ ለሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች በቀን አንድ ጊዜ እንዲመገቡ ከማድረግ ባሻገር የስልጠና እና የምክር አገልግሎትም እንዲያገኙም ተደርጓል ፡፡

የመሪነት ብቻ ሳይሆን የእናትነት እና የእህትነት ድንቅ ተግባር በተጨባጭ የታየበት፤ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑ የተረጋገጠብት በዚህም የተገፉ፤ የተረሱና ተሰፋ ቆርጠው የነበሩ ተስፋቸው ወደ ሚጨበጥ ለውጥ የተሻገረበት ይህ ሰዉ ተኮር ስራ በምድራዊዉ ሆነ በሰማያዊዉ ዓለም የሚያስመሰግን ክቡር እና ህያዉ ተግባር መሆን ችሏል፡፡

ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም በሃገር እና በትዉልድ ግንባታ ላይ ገንዘባቸዉን፤ እዉቀታቸዉን እና ጉልበታቸዉን ሳይሰስቱ በሁለተናዊ የልማት ስራዎች ላይ እየተሳተፉ ያሉ ዉድ ኢትዮጵያዉያን የነበረንን የመደጋገፍ እና አብሮ የማደግ እሴታችንን በፅኑ መሰረት ላይ ያቆሙ፤ታሪካዊ ኃላፊነታቸዉን የተወጡ ሲሆን ሌሎቻችንም ከዚህ በበለጠ ዘለቄታዊነት ባለዉ መልኩ አጠናክሮ ማስቀጠል የቀጣይ ስራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ባጋራው መልእክት አሳውቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review