ኤዲንሰን ካቫኒ ጫማውን ሰቀለ

You are currently viewing ኤዲንሰን ካቫኒ ጫማውን ሰቀለ

AMN ታኅሣሥ 19 ቀን 2018 ዓ.ም

ኤዲንሰን ካቫኒ ጫማ መስቀሉን ይፋ አደረገ። በእግርኳስ ከታዩ ምርጥ አጥቂዎች እንደ አንዱ የሚቆጠረው ካቫኒ ከዚህ በኋላ በተጫዋችነት ወደ ሜዳ እንደማይመጣ ገልጿል።

ዳኑቢዮ በተሰኘ የሀገሩ ኡራጋይ ክለብ የጀመረው የእግር ኳስ ሕይወቱ በአምስት የአውሮፓ ክለቦች አድምቆታል።

ፓሌርሞ ፣ ናፖሊ ፣ ፓሪሰን ዠርማ ፣ ማንችስሲዩናይትድ እና ቫሌንሲያ በአውሮፓ የተጫወተባቸው ክለቦች ናቸው።

የ38 ዓመቱ የቀድሞ ተጫዋች በተለይ በናፖሊ እና ፓሪሰን ዠርማ ስኬታማ ጊዜ አሳልፏል። በናፖሊ ኮፓ ኢታሊያን ሲያገኝ ፣ በፒ ኤስ ጂ 20 ዋንጫዎችን አሸንፏል።

ቫሌንሲያን ከለቀቀ በኋላ የአርጀንቲናውን ቦካ ጁኒየርስ የተቀላቀለው ካቫኒ ለሀገሩ ኡራጓይ 138 ጨዋታዎችን አከናውኗል።

በአጠቃላይ በእግርኳስ ሕይወቱ ባደረጋቸው 730 ጨዋታ 400 ግቦችን በስሙ አስመዝግቧል።

በአልማዝ አዳነ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review