ኢትዮጵያ እያደረገች ባለችው ሁለንተናዊ እድገት በየዘርፍ የሂሳብ ትምህርትን ማስፋፋት ይገባል

You are currently viewing ኢትዮጵያ እያደረገች ባለችው ሁለንተናዊ እድገት በየዘርፍ የሂሳብ ትምህርትን ማስፋፋት ይገባል

AMN – ታኀሣሥ 20/2018 ዓ/ም

ኢትዮጵያ እያደረገች ባለችው ሁለንተናዊ እድገት በየዘርፍ የሂሳብ ትምህርትን ማስፋፋት ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ተናገሩ።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመቱን በተለያዮ ፕሮግራሞች እያከበረ ይገኛል። ዮኒቨርስቲው በዛሬው ዕለት 75 ዓመታትን ከዩኒቨርሲቲው ጋር አብሮ የተጓዘውን የሂሳብ ትምህርት ክፍል የ75 ዓመታት የስኬት ጉዞና እድገትን የተመለከተ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) አዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ 75ኛ ዓመቱን ሲያከብር ዓመታትን ለመዘከር ብቻ ሳይሆን የተለያዮ ዓላማዎችን በማንገብ እንደሆነ የገለፁት፤ በተለይም ኢትዮጵያ እያደረገች ባለችው ሁለንተናዊ እድገት በየዘርፍ የሂሳብ ትምህርትን ማስፋፋት ይገባል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ የሂሳብ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ሳሙኤል አሰፋ (ዶ/ር)፤ በበኩላቸው የሂሳብ ትምህርት ለሀገር የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ ለማጉላት በዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት እንዲሁም ያሉ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል ይገባል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ይህንንም ለማድረግ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የሂሳብ ሙሁራን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡

የፓናል ውይይቱ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በሀገርና በውጭ ሀገራት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሩ የሂሳብ ሙሁራን እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review