ለከተማዋ ሰላም እና ደህንነት የሰላም ሰራዊት ተሳትፎ ትልቅ ሚና እንዳለው ተገለፀ

You are currently viewing ለከተማዋ ሰላም እና ደህንነት የሰላም ሰራዊት ተሳትፎ ትልቅ ሚና እንዳለው ተገለፀ

AMN ታኅሣሥ 21 ቀን 2018 ዓ.ም

የከተማዋን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ ተልዕኮ ላይ ነዋሪውን የሰላሙ ባለቤት ለማድረግ የሰላም ሰራዊት ተሳትፎ አይተኬ ሚና እንደሚጫወት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገለፁ።

6ኛው ዙር ከተማአቀፍ የሰላም ሰራዊት የንድፈሃሳብና ወታደራዊ ስልጠና በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተማ መሰጠት ጀምሯል።

በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የሰላምና ፀጥታ አደረጃጀቶችን በተለይም የሰላም ሰራዊት አባላት በመፍጠር እና በማደራጀት እንዲሁም ከመደበኛ የፀጥታ ተቋማት ጋር በማስተሳሰር የከተማዋን ሰላም አስተማማኝ ማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት በንቃት እየተከናወኑ እንደሚገኝ በመድረኩ ተነስቷል።

በስልጠናው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ አዲስ አበባ ሰላሟን ማረጋገጥ በመቻሏ በነዋሪዎቿና በጎብኝዎቿ ተመራጭና ተወዳጅ ከተማ ለመሆን ችላለች ብለዋል።

በዚህም በአጭር ጊዜ በርካታ ዓለማቀፍ ጉባኤዎችን በስኬት ማከናወን መቻሏ እንደአንድ ማሳያ ነውም ብለዋል።

ይህን አስተማማኝ ሰላም ዘላቂ ለማድረግ በየጊዜው የሚሰጡ የእጩ ሰላም ሰራዊት ስልጠና ትልቅ አቅም እንደሆነ የጠቀሱት ወ/ሮ ሊዲያ አሁን የተጀመረው በ6ተኛው ዙር የሰላም ሰራዊት ስልጠና በከተማ ደረጃ ከ22 ሺህ በላይ እጩ አዲስ አባላት ስልጠናውን እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ገ/ሚካኤል አሁን በስልጠና የሚያልፈው ኃይል ከዚህ ቀደም ስልጠና ወስዶ ስምሪት ላይ ከሚገኘው የሰላም ሰራዊት ጋር በማስተሳሰር የክ/ከተማውን ብሎም የከተማውን ሰላም ለማረጋገጥ አጋዥ ሀይል ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል።

በታምሩ ደምሴ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review