አዲስ አበባ የብልጽግና ፓርቲ ተግባራዊነት ሕያው ምስክር ናት

You are currently viewing አዲስ አበባ የብልጽግና ፓርቲ ተግባራዊነት ሕያው ምስክር ናት

AMN ታኅሣሥ 23/2018

የብልፅግና ፓርቲ ሀሳቦችና ንድፎች በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር የተረጋገጡ ናቸው ለመሆናቸው አዲስ አበባ ሕያው ምስክር ናት ሲሉ የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ገለጹ።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ በሞዴል የብልፅግና ኅብረቶች መካከል የሚደረግ የልምድ ልውውጥና ከተማ አቀፍ የአሸናፊዎች አሸናፊ የማጠቃለያ ውድድር በቦሌ ክፍለ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

የብልጽግና ፓርቲ የማኅበረሰቡን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን በቅርብ በመከታተልና በመፍታት በጠራ ሀሳብ የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በመዲናዋ በርካታ ተግባራት ስለማከናወኑ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ተናግረዋል።

ፓርቲው ሀሳቦችና ንድፎች በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር የተረጋገጠበት ለመሆኑ አዲስ አበባ ሕያው ምስክር ናት ያሉት አቶ ሞገስ ባልቻ ይህም የነዋሪዎቿን የዘመናት የመሠረተ ልማት ጥያቄ ከመፍታትም ባሻገር ለአፍሪካ ምሳሌ የሆነች የብልፅግና ተምሳሌት አዲስ አበባን መፍጠር ተችሏል ብለዋል።

ውድድሩ የፓርቲው አባላት ከተሰጣቸው ተልዕኮ አንጻር የማኅበረሰባቸውን ችግር ዘልቆ በማየትና በመከታተል እንዲፈቱ ያደረጉትን ጥረት የሚፈትሽ ነው ያሉት አቶ ሞገስ ባልቻ ዛሬ ላይ ምን ሠራን፥ ነገስ ምን መሥራት ይጠበቅብናል የሚለውን የምንለይበት ነው ብለዋል።

የማጠቃለያ መርሐ ግብሩ “ጠንካራ ኅብረቶች ለጠንካራ ፓርቲ ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ ያለው።

በራሔል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review