የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አንዳስታወቁት በውይይታቸው ወቅት ልባዊ የሆነ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውን ለፕሬዝዳንቱ ማስተላለፋቸውን አስታውቀዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት ላይ በመመስረት፣ መሪዎቹ በወቅታዊ እና በቀጣይ የሁለትዮሽ ትብብር መስኮች ላይ ተወያይተዋል።
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ፕሬዝዳንት ማክሮን የጋራ ፍላጎት ባላቸው ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ በየጊዜው መረጃ ለመለዋወጥ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።