ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአረንጓዴ አሻራ አካል የሆነው የሻይ ልማት ኢኒሺዬቲቭ ተከላው በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት የአረንጓዴ አሻራ አካል የሆነው የሻይ ልማት ኢኒሺዬቲቭ ተከላው በጥሩ ሁኔታ እየተከወነ ነው ብለዋል።
በመትከል የታየው መልካም ጅማሮ በአግሮ–ፕሮሴሲንግ ከተደገመ ሙሉ ስለሚሆን የግሉ ዘርፍ እሴት በማከል ቢሳተፍ ከሀገር ውስጥ ፍጆታ በተጨማሮ በኤክስፖርት ሀገራችንን ተጠቃሚ ያደርጋታል ሲሉ ገልጸዋል።