ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጂቡቲ ፕሬዝደንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ ጋር ጂኦ-ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ጨምሮ በቀጣናዊ ሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ተወያዩ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጂቡቲ ፕሬዝደንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ ጋር ጂኦ-ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ጨምሮ በቀጣናዊ ሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ተወያዩ

AMN ጥር 3/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጂቡቲ ፕሬዝደንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ ጋር በጆኦፖለቲካል ጉዳዮች: በቀጣናዊ ሰላምና ጸጥታ እንዲሁም በሁለቲዮሽ ትብብሮች ዙሪያ መወያየታቸዉን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ ጠዋት ጂቡቲ ስደርስ ፕሬዝደንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ አቀባበል አድርገውልኛል ብለዋል።

ውይይታችን በጆኦፖለቲካል ጉዳዮች፣ በቀጠናዊ ሰላም እና ፀጥታ ብሎም የሁለትዮሽ ትብብራችንን በተለይም በንግድ፣ ሎጂስቲክስ እና የልማት ሥራዎች በምናጠናክርበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነበር።

ይህም ለሰላም እና መረጋጋት፣ የኢኮኖሚ ትስስር እና የጋራ ብልጽግና ያለንን የወል ጽኑ አቋም የሚያመለክት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review