የትዉልድ ድምጽ የሆነዉ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ለ20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል የሀገር ገፅታን በሚገነባ መልኩ ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ላደረገው አስተዋፅኦ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት እውቅና ተሰጥቶታል፡፡
የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአል ስኬታማ ሆኖ እንዲከበር የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች ልዩ ዕውቅና እና ምስጋና ሰጥቷል፡፡
የትዉልድ ድምጽ የሆነዉ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክም 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ሕብረብሔራዊ አንድነቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት እንዲከበር ላደረገዉ የላቀ አስተዋጽኦ እዉቅና ተሰጥቶታል፡፡

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ እዉቅናዉን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር እጅ ተቀብለዋል፡፡
20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአል በኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነትና በማእከላዊ ኢትዮጵያ አስተናጋጅነት “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ በሆሳእና ከተማ መከበሩ ይታወቃል፡፡
በቤተልሔም አየነው