ኢትዮጵያ ያላትን የማኅበራዊ ካፒታል (Social Capital) እንደ ሀብት የማያይ ተቋምም ሆነ ሀገር ወደፊት መራመድ አይችልም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የፋይናንስ እምርታ በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ከተሳታፊዎች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው፣ ኢትዮጵያ ያላትን ትልቅ ሀብት (ማኅበራዊ ካፒታል) እንደ ሀብት የማያይ ተቋምም ሆነ ሀገር ወደፊት መራመድ አይችልም ነው ያሉት ።

እያንዳንዱ ፈጠራ የሚመነጨው ካለው ችግር መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የእኛን ‘ዕቁብ’ ያለበትን ችግር አይተን ባንክ ካልፈጠርን፣ የባንክ ሥርዓታችንን አይተን ‘ፊንቴክ’ ካላከልን፣ እንዲሁም የፋይናንስ ሥርዓቱን ውስንነት ተረድተን ‘ስቶክ ማርኬት’ ካልመሠረትን ፍላጎትና አቅርቦትን ማመጣጠን አይቻልም በማለት ገልጸዋል።
ማኅበራዊ ካፒታል ያስፈልጋል ሲባል የሌላውን እንዳለ መቅዳት እንዳልሆነና ይልቁንም በእኛ ዕውቀት፣ ባሕል እና ፍላጎት ላይ ተመስርተን ቴክኖሎጂን መተግበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የሀገርን መሻት፣ አቅምና የተፈጥሮ ሀብትን መሠረት ያደረጉ፣ እስከ አሁን የተዘነጉ ሀብቶች ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዲቀየሩ እንፈልጋለን ሲሉም ገልጸዋል።
በፍሬሕይወት ብርሃኑ