የከተራና የጥምቀት በዓል በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።
ሕብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሚሆኑ አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ሲመለከት ጥቆማ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርቧል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ በመላው ኢትዮጵያ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የከተራና የጥምቀት በዓል በስኬት እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት አካላት ጋር በመቀናጀት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ሰፊ የሰው ኃይል በማሰማራት ወደ ሥራ መግባቱን አስታውቋል፡፡
ሕብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሚሆኑ አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ሲመለከት የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp) በመጠቀም ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 በመደወል ጥቆማ በመስጠት ወይም መረጃውን በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት በማድረስ የዜግነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ እንዲሆን ተመኝቷል።