ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ደንቢ ኢኮ ሎጅን በይፋ መርቀዋል

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ደንቢ ኢኮ ሎጅን በይፋ መርቀዋል

AMN – ጥር 10/2018 ዓ.ም

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለትውልድ ሥራ የመጀመሪያው መዳረሻ የሆነው እና በ36.7 ሄክታር የጥብቅ ደን እና የተፈጥሮ ኃብት ስጦታ የተዘረጋው ደንቢ ኢኮ ሎጅ በይፋ ተመርቋል።

ኢኮ ሎጁ የሀገራችን የቱሪዝም ዘርፍ ባለፉት ሰባት አመታት ዘላቂነትን፣ የቅርስ ኃብትን እና ለዘመናት የሚዘልቅ ዓለም አቀፍ ደረጃን የመጠበቅ እድል መፍጠርን በማዋሃድ ምን ያህል እንደተለወጠ ማሳያ ነው።

የገበታ ለትውልድ ሥራ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቁ መዳረሻዎችን በማልማት የሀገራችንን እምቅ አቅም ለማውጣት የሚደረገው የሰፊው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ስትራቴጂ አካል ነው።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጀመረው ይኽ ሥራ በስኬት ከተተገበሩት የገበታ ለሸገር እና ገበታ ለሀገር መርሃ ግብሮች የቀጠለ እና ሥራዎቹን ወደ አዳዲስ አካባቢዎች የወሰደ ሲሆን የተፈጥሮ ውበትን፣ የባሕል ቅርስን እና ዘላቂ ልምድን በማቀናጀት የተከናወነም ነው።

እነዚህ ሥራዎች የከተማ እና ተፈጥሯዊ መዳረሻዎችን ወደ ሳቢ የቱሪዝም ማዕከልነት የለወጡ መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያሳያል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review